Skip to main content

በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ 1333/2016 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1073 /2017 ላይ ስልጠና ተሰጠ

የፌዴራል መንግስት ግዥ አገልግሎት

ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ለመንግስት ግዥ አገልግሎት የማኔጀመንት አባላት፣ ለግዥ ፈፃሚ ባለሙያዎች፣ የግዥ አፅዳቂ ኮሚቴ አባላት፣ ለፋይናንስ አስተዳደር ባለሙያዎች እና ሌሎች ለሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች  በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር  አዋጅ 1333/2016 እና አዋጁን ለማስፈፀም በወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያ 1073 /2017 ላይ  ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

የስልጠናው ዋና ዓላማ ሰልጣኞች በአዋጁም ሆነ የግዥ አፈፃፀም መመሪያው ላይ ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በግዥ መርሆዎች ስርዓቶች ላይ ውጤታማ የግዥ አፈፃፀም እንዲኖር ታስቦ መሆኑ ታውቋል።

ስልጠናውን የሰጡት በመንግስት ግዥ አገልግሎት የኢዩ ፕሮጀክት ከፍተኛ ልዩ  አማካሪ አቶ ታደሰ ከበደ ሲሆኑ፤ በመሠረታዊ የግዥ የህግ ማዕቀፎች፣ የግዥ ዘዴዎች ፣ ስልቶችና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ገለፃና ማብራሪያ አድርገዋል።

በስልጠናው ከግዥ ጋር ተያይዞ በተቋሙ ያለውን ነባራዊ ሁኔታና እያጋጠሙ ያሉ ጉዳዮችን አስመልክቶ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጉዳዮች  በአቅራቢው በኩል ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የስልጠናው ተሳተፊዎችም ይህን ስልጠና መውሰዳቸው በመንግስት የግዥ አፈፃፀም ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመው በቀጣይ ሰፋ ያለ ጊዜ ተወስዶ በመመሪያው ላይ በቂ ግንዛቤ ሊያዝ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት በመንግስት ግዥ አገልግሎት የግዥና ውል አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ክፍሌ ገ/ማርያም እንዳሉት ፤ተቋሙ  ትልልቅ ግዥዎችን የሚፈጽም ተቋም እንደመሆኑ በግዥ አዋጅና መመሪያዎች ላይ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ መያዝ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም የዛሬውን ስልጠና እንደ መነሻ በመውሰድ በቀጣይ ሰፋ አድርጎ ማንበብና አቅምን ማጎልበት ተገቢ መሆኑን ገልጸው መሰል የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችም በቀጣይ ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚሰጡ  አመላክተዋል።

በሌላ በኩል በመድረኩ ከግዥ ጋር ግንኙነት ያላቸው አነቃቂና አስተማሪ የሆኑ ነጥቦች በአገልግሎቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ኢቲሳ ደሜ ቀርቧል።

Add new comment

Restricted HTML

  • You can align images (data-align="center"), but also videos, blockquotes, and so on.
  • You can caption images (data-caption="Text"), but also videos, blockquotes, and so on.

About

We are transforming procurement into a strategic instrument for sustainable economic growth.

Featured Posts

Contact info

Contact information Federal Public Procurement Service (FPPS).