በተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት ላሉ ህጻናትና ወላጆቻቸው ድጋፍ ተደረገ
በተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት ላሉ ህጻናትና ወላጆቻቸው ድጋፍ ተደረገ
ዜና፡ አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት አመራሮች እና ሠራተኞች የህፃናት፣ የፆታዊ ጥቃት እና የአካል ጉዳተኞች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንስር ድርጅት በመገኘት የአልባሳትና ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።
በአገልግሎቱ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ ወ/ሮ እታለማሁ ጥላሁን በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት ከተቋሙ አመራሮች እና ሠራተኞች የተሰበሰቡ የተለያዩ አልባሳትና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ለማዕከሉ አስረክበዋል፡፡
ተስፋ አዲስ ፓረንትስ ቻይልድሁድ ካንሰር ድርጅት በካንሰር የተያዙ ህፃናትን ከወላጆቻቸው ጋር በመያዝ ተገቢውን ሕክምና እና እንክብካቤ በማድረግ የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩ ለማድረግ የሚሰራ ግብረሰናይ ድርጅት ነው፡፡
አገልግሎቱ በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን ከአሁን በፊትም የተቋሙን አመራሮችና ሠራተኞች በማሳተፍ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል እና ለሴቶች ማረፊያና ልማት ማህበር ከ2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ አልባሳትና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡