Skip to main content

“የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናትን መንከባከብና ብሩህ ተስፋ ሰንቀው እንዲያድጉ ማድረግ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡” ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ

“የነገ ሀገር ተረካቢ ህጻናትን መንከባከብና ብሩህ ተስፋ ሰንቀው እንዲያድጉ ማድረግ ከሁላችን ይጠበቃል፡፡” ዋና ዳይሬክተሩ ክቡር አቶ አስማረ ይገዙ

ዜና፡ አዲስ አበባ ጥር 01 ቀን 2018 ዓ.ም የመንግስት ግዥ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በዛሬው ዕለት በአገልግሎቱ የህጻናት ማቆያ ክፍል በመገኘት የአገልግሎቱን ሰራተኞች ህጻናት ልጆች እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎች 6 ህጻናትን የእንኳን አደረሳችሁ እና የስጦታ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

በፕሮግራሙ የአገልግሎቱን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ ይገዙን ጨምሮ ም/ዋና ዳይሬክተሮች፣ የማኔጅመንት አባላት እና የህፃናት ወላጆች ተሳትፈዋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ አስማረ እንዳሉት የነገዋን ኢትዮጵያ የሚረከብ ንቁ ትውልድ ለመተካት ህጻናትን በመንከባከብ ደስተኛ እና ጤነኛ ሆነው እንዲያድጉ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

አቶ አስማረ አክለውም የአገልግሎቱ አመራርና ሠራተኞች በፈቃደቸው ከወር ደመወዛቸው እንዲቆረጥ በማድረግ ከአገልግሎቱ ሰራተኞቸ 8 ልጆች በተጨማሪ በአቅራቢያ ለሚገኙ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ ነዋሪዎች 6 ህፃናት በየወሩ ከ950 ብር በላይ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ በመግለፅ፤የዛሬው የስጦታ ፕሮግምም የማኔጅመንት አባላትን በማሳተፍ የተደረገ መሆኑን አንስተው ይህንን ላደረጉ አመራሮችና ሠራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የህጻናት ወላጆችም በበኩላቸው እየተደረገ ባለው የገንዘብ ድጋፍ፤ እንዲሁም በዛሬው እለት በተደረገው የእንኳን አደረሳችሁ እና የስጦታ ፕሮግራም እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን በመግለጽ የአገልግሎቱን አመራሮችና ሠራተኞች አመስግነዋል፡፡

 

“Caring for children—the heirs of our nation’s future—and enabling them to grow with bright hope is a responsibility that rests on all of us,” said the Director General, H.E. Mr. Asmare Yigezu.

News: Addis Ababa, Tir 01, 2018 E.C.

On the occasion of the 2018 Ethiopian Christmas celebration, the Public Procurement Service organized a Christmas greeting and gift-giving program today at the Service’s childcare center. The program benefited the children of the Service’s employees as well as six children from nearby low-income households.

The event was attended by the Director General of the Service, H.E. Mr. Asmare Yigezu, Deputy Directors General, members of management, and parents of the children.

Speaking at the program, the Director General, H.E. Mr. Asmare Yigezu, stated that in order to nurture an active generation that will inherit Ethiopia’s future, it is essential to care for children and ensure that they grow up healthy, happy, and well-supported.

Mr. Asmare further explained that the Service’s management and employees have voluntarily agreed to contribute a portion of their monthly salaries to support children. Through this initiative, in addition to supporting eight children of the Service’s employees, the Service is providing monthly assistance of more than 950 birr to six children from nearby low-income families. He also noted that today’s gift-giving program was carried out with the active participation of management members and expressed his appreciation to the leaders and staff who made this support possible.

Parents of the children, in turn, expressed their great happiness with the ongoing financial support as well as with today’s Christmas greeting and gift-giving program, and extended their heartfelt thanks to the Service’s leadership and employees.

 

 

Add new comment

Restricted HTML

  • You can align images (data-align="center"), but also videos, blockquotes, and so on.
  • You can caption images (data-caption="Text"), but also videos, blockquotes, and so on.

About

We are transforming procurement into a strategic instrument for sustainable economic growth.

Featured Posts

Contact info

Contact information Federal Public Procurement Service (FPPS).